በኢትዮጲያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 113 ደም አፋሳሽ ግጭቶች መከሰታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናገሩ፡፡

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ 113 ደም አፋሳሽ ግጭቶች ተከስተዋል ብለዋል።

በኦሮሚያ 37 ደም ያፋሰሱ ያፈናቀሉ እና ንብረት ያወደሙ ግጭቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

በአማራ 13 ደም ያፋሰሱ ግጭቶች እደነበሩ ጠቅሰው በተለይ በወልቃይት በቅንማንት ስም የተከሰተውን አንስተዋል፡፡

በቤኒሻንጉል እንዲሁም 15 የተከሰቱ ሲሆን በተለይ በመተከል ፤በዳንጉር የደረሱትን መጥቀስ ይቻላል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ደግሞ 14 የደረሰ ሲሆን በተለይ ከአርቲስት ሀጫሎ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዙ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጀምሮ እውቅ ሰዎችን ለመግደል ታስቦ እንደነበር አንስተዋል።

በጋምቤላ የስደተኞችን ካምፕ ጨምሮ 7 ግጭቶች ተከስተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በደቡብ ክልል በኮንሶ በጌድዮ በጉራ ፈርዳ ንጹሀን እንዲገደሉ ንብረት እንዲወድም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በጅጅጋ ፤አፋር ፤ድሬዳዋ ፤ሲዳማ እና ሀረሪም እንዲሁ ግጭቶች እንደነበሩ አንስተው በዚሁሉ ውስጥ ግን አንድም ቀን በትግራይ ግጭት ተከስቶ አያወቅም ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

በዚያ አንድ ቀን ኩናማ ከትግራይ ፤ኢሮብ ከትግራይ መጋጭት የለበትም ግን በሌላው የሆነው ተከስቶ አያውቅም ያ የሆነው ደግሞ ይህንን የሚፈጥሩት አካላት ፍላጎት ስለሌላቸው ነው ብለዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.