ሊኒየነር አክስሌሬተር የተባለ የካንሰር ጨረር ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ መሳሪያ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ተተክሏል፡፡
ወጪው ሙሉ በሙሉ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሸፈነ ሲሆን የካንሰር የጨረራ ህክምና አገልግሎት የሚሰጠውም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሆኑ ተነግሯል፡፡
የተተከሉት የህክምና መሳሪያዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተለያዩ ቦታዎች መሆኑም ተነግሯል፡፡
ይህ አገልግሎት በኢትዮጵያ መጀመሩም የካንሰር ህክምና አገልግሎትን ከፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጻል፡፡
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከዚህ በፊት የነበሩ የካንሰር ሀኪሞች 4 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም 8 ናቸው ተብሏል፡፡
የጨረራ ህክምና በተፈጥሮ እጅግ ውድ የሆነ አገልግሎት ነው ፣ በአሁኑ ሰዓት ይህ አገልግሎት መጀመሩ ለተገልጋዮች እፎይታ ይሰጣል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የጨረራ ህክምና በ1992 የተጀመረ ሲሆን በ1997 ደግሞ የጨረራ ማዕከል መከፈቱ ተሰምቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የካንሰር የጨረራ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ መሳሪያ የtተከለ ሲሆን በስነ ሥርዓቱ ላይ የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት ሮማን ተስፋዬ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ተገኝተዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በሔኖክ ወልደገብረኤል
ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም











