ከሰሞኑ በኮንሶ ዞን፣ አማሮ፣ ዴራሼ፣ አሌና ቡርጂ ወረዳዎች ባሉ ግጭቶች የተጠረጠሩ 137 ሰዎች ተያዙ።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ህዝቡ እርስ ችግር ባይኖርበትም ነባር ጥያቄዎችን ሰበብ በማድረግ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች አማካኝነት በ17 ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት የ66 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም በዚህ ግጭት ሳቢያም 39 ሰዎች የአካል ጎዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ130 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል ብለዋል።

በአካባቢው የህወሃትና ኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት የተፈጸመውን ጥቃት በመፍራትም ከ130ሺ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አስረድተዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ለእነዚህ ወገኖች አሰቸኳይ የእለት እርዳታ እየቀረበላቸው መሆኑንም ሀላፊው ይናገራሉ፡፡

በአካባቢው የህግ የበላይነትን ለማስከበርም 4 የምርመራ ቡድኖች ተቋቋመው መረጃዎች እየተሰባሰቡ መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ እና የወረዳዎቹ ነዋሪዎች ባደረጎት ከፍተኛ ጥረትም ግጭቱ እንዲነሳ ተሳትፎ ያደረጉ 137 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቀሪዎቹን የጥፋት ቡድን አባላት ህግ ፊት የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *