የለውጥ ሃይሉን ተክትሎ የተፈጸሙ ችግሮችን በአስቸኳይ ለማስቆም የሚያስችል ስልጣን እና ዕድል እንዳልነበራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ጋር ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

ከጥያቄዎቹ መካከልም እርሳቸው ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ላይ ለምን ቀድመው የህወሃትን ጥፋት አላስቆሙም ነበር? አንዱ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም “እኔ ራሴ በወቅቱ ዘመናዊ እስር ቤት ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል በመልሳቸው፡፡

ሃገር እና ህዝብ የሚጠብቅብኝን ሃላፊነት መወጣት ለመቻል ቤተሰቦቼን ወደ ውጪ ሸኝቼ ለሁለት ወራት ያህል ራሴን ነጻ ለማውጣት ትግል አድርገናል ብለዋል፡፡

በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች ጋር በመነጋገር ለውጡ እንዳይቀለበስ ህዝቡም እንዲረዳ ለማድረግ በድፍረት ለመውጣት ሞክረናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በሶማሊያ ክልል በቀድሚያ ጎዙ አድርገናል ፡፡ያ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ኢትዮጲያን የማፍረስ እቅዱ መጠንሰሻ በመሆኑ ነውም ብለዋል፡፡

በመቀሌም፤ በአንቦ ፤በጎንደር እና ባህርዳር ለመሄድ ስንነሳ አንዴ ኦነግ ሁለትም የወልቃይትና የቅማንት አስመላሽ ኮሚቴ ሊገልህ ይፈልጋል ተብዩ ነበር ግን አልፊ ሄጃለሁ፡፡

በኃላም በተለይ በሶማሊ እና በትግራይ የተደረገልንን አቀባበል ስመለከት የጁንታው ቡድን ደንግጧል ብለዋል፡፡

በኃላም ከእስረኞች መፈታት በተለይ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጊ መፈታት ጋር በተያያዘ ልዩነታችን ለየለት ነው ያሉት ፡፡

ለውጡ አጥፉዎችን በአፋጣኝ ለማስቁም የነበረበትን ፈታና አብራርተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 21 ቀን 2ጠ013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *