በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ኢዴፓ ለነገ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተንዛዛ አሰራር ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ እንዳስታወቀው ለነገ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የያዝነው ፕሮግራም ተሰርዟል ብሏል። ፓርቲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላለፈብንን የስረዛ ውሳኔ አስመልክቶ ለነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቶ ነበር።መግለጫ ሊሰጡበት በታሰበው ሆቴሉ አካባቢው ያለው የካራማራ ፓሊስ ጣቢያ ፈቃድ አምጡ አለን እዛ ሄድን እነሱ ደግሞ ለቦሌ ክ/ከተማ ፓሊስ መምሪያ […]