አልጄርያ ሙስና ሰርተዋል ያለቻቸው ሁለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮቿ ላይ የአምስት አመት እስር ፈርዳባቸዋልች፡፡
የአልጄርያ ፍርድ ቤት የሀገሪቷን የቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሮች በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ተጠያቂ ናቸው ያላቸው ሲሆን እስከ አምስት አመት የሚሆን ፍርድ ፈርዶባቸዋል፡፡
አህመድ ኦውያሂያ እና አብደልማሌክ ሴላል ከቴሌኮም ኩባንያዎች ጋር ህገ ወጥ ድርድር አድርገዋል በሚል ነው የተከሰሱት።
ሁለቱ ባለስልጣናት በፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ የስልጣን ዘመን ሲሆን ያገለግሉ የነበሩት ፤ ዲሞክራሲ እንሻለን በሚል አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ነበር ከስልጣን የተባበረሩት፡፡
ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሌሎች የሙስና ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በእስር ቤት የሚገኙ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሔኖክ አስራት
ሕዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም











