በመተከል ዞን 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ጦር መሳሪያ ይዘው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋና ኢንጂፈታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በመተከል ዞን የሚገኙ የጥፋት ቡድኖች ለክልሉ መንግስት እጅ እንዲሰጡ በቀረበው ጥሪ መሰረት እስከ ትናንት ድረስ ዳንጉር ወረዳ ላይ ይንቀሳቀሱ የነበሩ 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች እጅ የሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ቡድኖችን የሚመሩ ግለሰቦች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል የሚሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በመሪዎቹና በተላላኪዎቹ መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ በተበታተነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ እጃቸውን ለመንግስት የሰጡት 43 ፀረ-ሰላም ሀይሎች በዚሁ የአሳብ ልዩነት እጅ ሊሰጡ እንደተገደዱ መረጃዎች አግኝተናል ብለዋል፡፡

እነዚህ ሀይሎች በዳንጉር ወረዳ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆኑ በሌሎችም ወረዳዎች የሚገኙ የጥፋት ቡድኑ ርዝራዦች እጅ በመስጠት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ እንደሚሉት ለጥፋት ቡድኑ ጥሪ የቀረበው የህዝብና የሀገር ድንነት ለማረጋገጥ እንደሆነ ጠቁመው የጥፋት ሀይሎች ጥሪውን ተቀብለው ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ ጠይቀው እጅ በማይሰጡት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

በደረሰ አማረ
ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *