ከኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር ለሚኖሩ የአፍሪካ ህጻናት የፍራፍሬዎች ጣዕም ያለው የጸረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት መሰጠት ሊጀመር ነው።

ከአፍሪካ ውጪ የሚኖሩ እና ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ህጻናት የተለያዩ ፍራፍሬዎች ጣዕም ያላቸውን የጸረ ኤች አይ ቪ ቫይረስ መድሃኒት ሲወስዱ ዓመታትን አስቆጥረዋል።

ይሁንና ወደ አፍሪካ ስንመጣ ግን ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ህጻናት በጣዕም ደረጃ በሌላው ዓለም ያሉ ህጻናት የተለየ የጸረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት እየወሰዱ ነው።

ይህ በመሆኑ ምክንያት ህጻናት መድሃኒቱን ላለመውሰድ መፈለግ እና ማቋረጥ እንዲጨምር እና እንዲሞቱ ሲያደርግ ቆይቷል።

ይሄንን ችግር ለመፍታት ሲባልም በኤድስ ለተያዙ ሕፃናት አነስተኛ ዋጋ ያለው እንጆሪ ጣዕም ያለው ታብሌት በአፍሪካ አገሮች በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት በዓለም ዙሪያ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ከኤች አይ ቪ ኤደስ ቫይረስ ጋር እንደሚኖሩ ያስታወቀ ሲሆን ህክምና የሚያገኙት ግን ግማሾቹ ብቻ ናቸውም ብሏል፡፡

በመሆኑን ከፈረንጆቹ 2021 ዓመት አንስቶ እነዚህ ጣዕም ያላቸው መድሃኒቶች ለህጻናቱ የደርሳሉ መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.