በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በየሳምንቱ ለምርመራ ከሚመጡ ዜጎች መካከል ከ120 በላይ ዜጎች በካንሰር ይያዛሉ ተባለ፡፡

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በየሳምቱ ለምርመራ ከሚመጡ ዜጎች ውስጥ ከ120 እስከ 150 የሚጠጉ ዜጎች በካንሰር እንደሚያዙ ነው የተገለጸው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አይናለም አብርሀ ካንሰር እና የጨረር ህክምና በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል ማብራርያ በሰጡበት ሰአት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡በመሆኑም በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝም ነው ዶ/ር አይናለም የተናገሩት፡፡

ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጡት የህዝቡ የአኗኗር ሁኔታ የህክምና እጥረት እና የአመጋገብ ባህሪያችን ዋነኞቹ ምክንያት እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ ከሚፈጠረው የካንሰር መጠን ወደ 33 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

በሴቶች ላይ 30 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡በወንዶች ላይ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ በሁለተኛ ደረጃ የፕሮስቴት ካንሰር እና ከተለያዪ እጢዎች የሚነሱ የካንሰር አይነቶችን ይጠቀሳሉ።

በኢትዮጵያካንሰር በርካቶችን በዋናነት ለህልፈት ከሚያበቁ ተላላፊ ያልሆኑ አራት በሽታዎች አንዱ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይገልፃል።በሀገሪቱ ትክክለኛ ምዝገባ ባለመኖሩ ምን ያህል ሰው በካንሰር እንደተያዘ ለማወቅ አደጋች እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.