ኢራን የተባበሩት መንግስታ ከፈቀደላት በላይ ዩራኒየም ለማበልፀግ የሚያስችላትን አዲስ ህግ አፀደቀች፡፡


በፖርላማው የፀደቀው አዲሱ ህግ እንደሚለው በባላንጣዋ አሜሪካ የተጣለባትን እቀባ በሁለት ወራት ውስጥ የማይነሳላት ከሆነ፤ በ2015 በኒክሌር ስምምነቱ ከተደረሰበትና ከተፈቀደላት 3.67 በመቶ ላይ ወደ 20 በመቶ ከፍ አደርገዋለው ብላለች፡፡
ነገር ግን ፕሬዝደንቷ ሀሰን ሮሀኒ የህጉን አተገባበር እንደሚቃወሙት ተናግረዋል፡፡
እርሳቸው እንደሚሉት ይህ እቅድ አደገኛና የዲፕሎማሲ ስራውን የሚያበላሽ ነው፡፡
የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት በበኩላቸው በዚህ ስራ ላይ ቁልፍ ሰው የነበሩት ታላቁ የሳይንስ ሊቅ በእስራኤል ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዩች መነጠቃቸው ህጉ በአሰቸኳይ እንዲተገበር የሚያስገድድ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለሲኤን ኤን እንዳሉት በሳይንቲስቱ ግድያ እስራኤል እጇ አለበት፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *