የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰጠ ነው

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች 73 ሺህ 45 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡

ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ባዮሎጂ ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ የህብረተሰብ ሳይንስ፣ ሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርቶች ናቸው፡፡በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ትምህርቶችን ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ ሲሰጥ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎችም እስከ ታህሳስ አጋማሸ ድረስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል እንደ አዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8
ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *