በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች በነጻ ለማስተማር ቃል እየገቡ ነው፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በቻሉት መጠን ለሃገር ክብር ዘብ የቆሙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች እንዲያሰተምሩ በጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የግል ተነሳሽነት በተጠየቁት ጥያቄ መሰረት በመጀመሪያ ጉዞው በሀዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆችን በነጻ ለማስተማር ቃል ገብተዋል፡፡

በሀዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙና ይህንን ዓላማ ለመደገፍ ቃል የገቡ የግል ትምህርት ቤቶችም እንዳላቸው የቅርንጫፍ ብዛት ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያስተምሩ ነው ለትምህርት ቤቶቹ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የቀረበው ይህ ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ የቻለው፡

ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገረው በሻሸመኔ የሚገኘው ሉሲ ትምህርት ቤት ባሉት አምስት የማስተማሪያ ቅርንጫፎች አንድ አንድ ተማሪ ለመቀበል ቃል ገብተዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን ተቀብለው በነጻ ለማስተማር ቃል ከገቡ የክልል ከተሞች ትምህርት ቤቶችም በሃዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙት ቢኤንቢ፣ ሉሲ፣ ዩኒየን ማውንት፣ ኦሊቭና ኤስ ኦኤስ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ይህንን መልካም ተግባር በአዲስ አበባና በክልል ከተሞችም እንዲቀላቀሉ የማስቀጠል እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *