የድርጅቱ መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ዳንኤል ዮሃንስ እንዳሉት፣ ”መንግስት ባመቻቸልን የቀረጥ ነጻ እድል መሰረት ከዚህ በፊት ለ5 ሺህ ሰዎች የዘመናዊ ታክሲ አገልግሎት ተጠቃሚና ባለቤት ማድረግ እንደተቻለ አውስተዋል።
አሁን ደግሞ ለደንበኞች በገባነው ዉል መሰረት አዳዲስ መኪናዎችን ወደ ሀገራችን ለማስገባት እና ለማስረከብ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ ብሏል።
በመቀሌ ጉምሩክ 126 መኪናዎች፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ 84 መኪናዎች፣ በጅቡቲ ወደብ 67 መኪናዎች፣ እንዲሁም በቀጣዮቹ 15 ቀናት ውስጥ የሚገቡ 174 መኪናዎች በጠቅላላው 451 መኪናዎችን ወደ ሃገራችን ለማስገባት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።
የእነዚህ ታክሲዎች ስራ መጀመር በተለይ ቱርሲቶችን ወይም የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን በማጓጓዝ ሀገራችን በቱሪዝም ዘርፍ እውቅናና ገቢም እንድታገኝ ይረዳሉ ሲሉ ተናግረዋል አቶ ዳንኤል።
በመሆኑም ሃገራችንን በዘርፉ ለማዘመን እንዲሁም በሀገራችን የተከሰተውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የኮቪድ 19 ያስከተከውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማካካስ በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን ለማገዝ በርትተን እንሰራለን ማለታቸውን ሪፖርተራችን ጅብሪል ሙሀመድ ዘግቧል።











