የታዛኒያው ፕሬዝደንት ሚኒስትሮቻቸውን ሰልፊ መነሳት እና ዋትስአፕ መጠቀም ከለከሉ::

የታዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአዲሱ የካቢኒ አባላት ራሳቸውን ሰልፊ በማሳት እና በዋስት አፕ በመላላክ ሚስጥር እንዳያወጡ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ይህንን የተናገሩት ረቡዕ ዕለት በዋና ከተማዋ ዶዶማ ውስጥ ሚኒስትሮችን እና ምክትላቸውን ቃለ ማሀላ እንዲያደረጎ በተደረገ አንድ ዝግጅት ላይ ነው ፡፡
ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ “መሀላችንን እንጠብቅ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ስነስርአት ላይ ቃለ መሀላ እንዲፈጽሞ ከሚጠበቁት መካከል የህዝብ እንደራሴም በቃለ ማሀላውን በአግባቡ መፈጸም ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡
እኚህ ተባራሪ የህዝብ እንደራሴ ፍራንሲስ ዱላኔ ሲባሉ በማዕድን ሚንስትር በተባባሪ ሚንስትርነት ነበር የተመረጡት፡፡

ይሆን እንጂ ተራቸው ደርሱ ወደ መድረኩ ቢወጡም የተሰጣቸውን ቃለ መሀላን መፈጸም ተቸግረው ነበር።
በቃለ መሀላው የተካተቱ አረፍተ ነገሮችን ለማንበብ ሲቸገሩ፣ ቃላት ለማውጣት ሲከብዳቸው ሲንተባተቡ የሚያሳይ የሶስት ደቂቃ ቪድዮ በትዊተር ተለቋል።
ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊ፤ ለሥራው ማመልከቻ ያስገቡ ሰዎችን የሥራ ልምድ ከገመገሙ በኋላ እንደመረጧቸው ተናግረዋል “ይህንን ሥልጣን ቃለ መሐላ በአግባቡ መፈጸም ለሚችል ሰው እሰጣለሁ” ሲሉ አሳውቀዋል፡፡

ስራቸውን በቃለ መሀላ ያጡት የህዝብ እንደራሴ ለምን ቃለ መሀላውን በአግባቡ ለመፈጸም እንደተቸገሩ አላብራሩም ብሏል ዘገባው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.