በኢትዮጵያ የሚገኝው የናሚቢያ ዲፕሎማት ባለቤት ሁለት ልጆቿን ገደለች፡፡

በኢትዮጵያ የናሚቢያ ኤምባሲ ውስጥ የዲፕሎማቱ ሚስት ሁለት ልጆቿን መግደሏልን ነው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያስታወቀው፡፡
የናሚቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሚገኙት የዲፕሎማት ልጆች ላይ ግድያ መፈጸሙን ለሀገራቸው ሚዲያ ለሆነው ናሚቢያን ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

የዲፕሎማቱ የህግ ሚስታቸው በገዛ ልጆቿ ላይ ግድያ መፈጸሟን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ሁለት ልጆቿ በደረሰባቸው ጥቃት ወዲያውኑ ሂወታቸው ሲያልፍ ሶስተኛው ልጅ ደግሞ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል እንደሚገኝ ነው ቢቢሲ አፍሪካ ያወጣው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

የናሚቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክለው እንደተናገሩትም በግለሰቧ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረው እስካሁን ድረስ ለእስር አለመደረጓን ተናግረዋል፡፡
እንደዚሁም ለዲፕሎማቱ ቤተሰቦች ከዚህ በኃላ ጥብቅ የሆነ ጥበቃ እንዲደረግ ሚኒስትሩ ትዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.