በቀድሞ ስሟ ስዋዚላንድ በመባል የምትታወቀው ስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አምብሮስ ድላሚኒ በ52 አመታቸው ሂወታቸው ማለፉን ነው የተነገረው፡፡
አምብሮስ ድላሚኒ ሂወታቸው ያለፈው በደቡብ አፍሪካ ህክምና እየተደረገላቸው ሳለ ነው ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሳምታት አክል በደቡብ አፍሪካ ሆስፒታል ከፍተኛ ህክምና እየተደረገላቸው ነበርም ተብሏል፡፡
በ2018 ወደ በትረ ስልጣኑ የመጡት አምብሮስ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነበር ወደ ስልጣኑ የመጡት፡፡
ወደ ስልጣኑ ከምምጣታቸው በፊት ለ18 አመታት ያህል በቴሌኮም ዘርፍ መስራታቸውን ነው ታሪካቸው የሚያሳየው፡፡
እንዲሁም በባንክ ኢንዱስትሪውም ለበርካታ አመታት እንደሰሩም ነው የተነገረው፡፡
በሀገሪቱ 6።ሺህ 700 ያህል ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 124 ሰዎች ደግሞ ሂወታቸው ማለፉን አልጀዚራ አፍሪካ ሲ ዲ ሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም











