ፑቲን በመጨረሻ ለባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደንን ዛሬ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ በመሆናቸው ለጆን ባይደን ከስድስት ሳምንት በኋላ እና የምርጫ ኮሌጁ በይፋ የባይደንን አሸናፊነትን ባረጋገጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት ያስተላለፉት ፡፡

የምርጫው ውጤት ከታወቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ የዓለም መሪዎች አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ባይደን እንኳን ደስ አሉት ሲሉ ፣ ፑቲን ግን ለአሸናፊው የእንኳን ደስ አሉ መልእክት ከማስተላለፋቸው በፊት ኦፊሴላዊ ውጤቱን መጠበቁ “ትክክል” ነው ብለው በወቅቱ ተናግረዋል ብሏል ሲኤን ኤ ኤን በዘገባው ፡፡

ቭላድሚር ፖቲን ለተመራጮ ፕሬዝዳንት ስኬት ተመኝተዋል፡፡

በዓለም ላይ በአሁኑ ወቅት እየገጠሟት ያሉትን በርካታ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ለመፍታት ልዩነቶች አሉ፡፡

ነገር ግን ለዓለም ደህንነት እና መረጋጋት ሲባል ይህንን ልዩ ሃላፊነት የሚሸከሙት ሩሲያ እና አሜሪካ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፑቲን “በእኩልነትና በጋራ መከባበር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ የሩሲያ-አሜሪካዊ ትብብር የሁለቱም አገራት ህዝቦች እንዲሁም የመላው ዓለም ማህበረሰብ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ነው” ብለዋል ፡፡

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን “እኔ በበኩሌ ከእርሶ ጋር ለመተባበር እና ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ” ብለዋል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *