ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ዝግጁ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ትብብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረበች ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንዲሁም የተለያዩ ሀጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጃንሜዳ የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ጃንሜዳ ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ከምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ትብብር በቤተክርስቲያኗ እና በህዝበ ክርስቲያኒቱ ስም አቡነ ማቲያስ ምስጋና አቅርበዋል ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የጥምቀት በዓል የሁሉም ኢትዮጵያውያን በዓል ፤የዓለም ቅርስ በመሆኑ ልንጠብቀው እና ልንንከባከበው ይገባል ብለዋል ።

በዓሉ የኢትዮጲያዊነት ባህል እና እሴት የሚጎላበት በመሆኑ የአካባቢው ወጣቾች ፣የስፖርት ቤተሰቡ እና አርቲስቶች ተባብረው ለበዓሉ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው ህዝበ ክርስቲያኑ ላሳየው ትዕግሥት እና ተሳትፎ ምክትል ከንቲባ አመስግነዋል ።

ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *