ዛሬ ረፋድ ላይ ቦሌ ኦሮሚያ ታወር አጠገብ እየተሰራ ካለ ህንጻ ላይ የወደቀ እንጨት እግረኞች ላይ ጉዳት አደርሷል፡፡

አራቱ ጓደኛሞች በህንፃው ስር ባለ የእግረኛ መንገድ ላይ እያለፉ ሳለ ነበር ከህንጻው ላይ የወደቀ እንጨት አግኝቷቸው አንዱን ለከፋ ጎዳት ሁለቱን ደግሞ ቀላል ጉዳት ያደረሰባቸው፡፡አንዱ ግን ከዚህ ጎዳት መትረፍ ችሏል፡፡

ሪፖርተራችን በስፍራው በመድረስ ከአይን እማኞች እንዳጣራው አሁን ጎዳት የደረሰባቸው ግለሰቡች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡በከተማችን እየተገነቡ ካሉ ይህንን መሰል ህንጻዎች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ባለመሆኑ መሰል አደጋዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡

በመሆኑም የህንጻ አሰሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቂ በሚገነቡበት ህንጻ አከባቢ እንዲወስዱ የሚመለከተው አካል ጥብቅ ክትትል ይገባዋል፡፡እግረኞችም በእነዚህ አከባቢዎች መንገድ ሲያቋርጡም ሆነ ሲጓዙ ፈጠን ብሉ መጓዝ አሊያም አማራጭ መንገድ መጠቀም ይገባቸዋል፡፡

ደረሰ አማረ
ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.