መጪዎቹ ወራት የአደባባይ በዓላት የሚበዙበት በመሆኑ ህብረተሰቡ እራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የጉባኤው ዋና ፀሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመግለጫቸው እንዳሉት፣ የሃይማኖት ተቋማት ከዚህ በፊት ኮቪድን ለመከላከል አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮችን ሲያደርጉ እንደነበር ገልፀው፣ በዚህም የእምነት ተቋማትን እስከመዝጋት ተደረሶ እንደነበር አውስተዋል።

አሁን ደግሞ ቫይረሱ ባህርይውን እየቀየረ በመጣበትና በተስፋፋበት ጊዜ፣ የእምነት ተቋማትን ጨምሮ ማህበረሰቡ እየተዘናጋ እንደሆነ ተናግረዋል።

ቀሲስ ታጋይ በቅርቡ የሰዎችን መሰባሰብ የሚጠይቁ ሃይማሞታዊ በአላት በተለይ በክርስትና እምነት እንደነ ቅዱስ ገብርኤል፣ ጥምቀትና ገና በአላት እየመጡ በመሆናቸው ከወዲሁ ልዩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት በጋራ ተወያይተው ከዚህ በኋላ ኮቪድን ለመከላለከ ሲባል ማንኛውም አማኝ በእምነት ቦታዎቹ ሊፈፅማቸው የሚገቡ 4 አይነት ጥብቅ መመሪያዎችን ማውቱን ጠቁመዋል።

በዚህም ሁሉሙ ኣማኝ ወደ ማምለኪያ ቦታወች ሲመጣ፣
1ኛ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ
2ኛ እጆቻቸውን በሳሙና እንዲታጠቡ
3ኛ አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁና
4ኛ ምንም አይነት መዘናጋት እንዳያሳዩ የሚሉ ናቸው።

እንዚህ መመሪያዎች ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የእምነት ተቋማት መተግበር እንዳለበቸውና ሁልጊዜም ቢሆን አማኞች ፀሎት ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በመግለጫው የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወሮ ሰሃረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፣ ኮሮናን ለመከላከል ሲባል መከልከል የሚከብደውን ሃይማኖታዊ ስርዓት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ግን ተቀበለው በመቆየታቸው የእምነት ተቋማቱን አመስግነዋል።

ወሮ ስሃረላ ኮቪድ 19 በሀገራችን እያደረሰ ያለው ጉደትና ሞት እየጨመር መሁኖን ጠቁመው፣ በዛው ልክ ደግሞ ሰዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ እየቀነሰ መጥቷል ብለዋል።

አሁን ደግሞ ገና በምርምር ያልታወቀ የኮሮና አይነቶች እየተከሰቱ ባሉበት ሰኣት መዘናጋቱ ዋጋ እንደሚያስከፍል ተናግርዋል።
ስለሆነም ከዚህ በኋላ ኮሮናን ለመከላከል የሚደረጉ ነገሮች እንደ አዲስ ሊተገበሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይ የማስክ አጠቃቀም፣ በየቦታው እጅን የመታጠብና የማስታጠብ፣ ማህበራዊ ርቀትን የመጠበቅ ላይ በእጅጉ መቀነሳቸውን ጠቁመዋል። በተለይ ከአዲስ አበባ ውጪ ደግሞ እነዚህ ነገሮች በብዛት እንደማይተገበሩ ተናግረዋል።

ስለሆነም ከዚህ በኋላ እነዚህ የመከላከያ መንገዶች በሁሉም ሰወች ዘንድ እንደገና እንደ አዲስ መተግበር እንዳለበቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *