በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ ተረከበ::

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አስታወቁ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፤ የንፁሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሜጀር ጄኔራሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋምና የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ “በመተከል ዞን የተጀመረው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *