ኃይለማርያምና ሮማን ፋዉንዴሽን በጂንካ ከተማ አዳሪ ትምህርት ቤት ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።

ፋውንዴሽኑ በደቡብ ኦሞ ዞን የሴቶችን መብትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ የውይይት መድረክ በጅንካ ከተማ አካሂዷል።

ውይይቱን ፋውንዴሽኑ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት፣ ከደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደርና ከፊንላንድ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

በዚህ መድረክ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋሞች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ 200 በላይ ውሳኔ ሰጪዎች ተሳትፈዉበታል፡፡

ፋውንዴሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በጅንካ ከተማ የአርሶና አርብቶ አደር ሴት ልጆች የሚማሩበት አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲገነባ መወሰኑን ገልጿል።

አዳሪ ትምህርት ቤቱ በአካባቢው ያሉ አርብቶ አደር ልጆችን በማስተማር የተሻለ እውቀት እንዲያገኙ በማድረግ አገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት ያስችላል ተብሏል።

አዳሪ ትምህርት ቤቱን አስመልክቶ የዲዛይን፣የግንባታ ወጪ እና ሌሎች ዝርዝር ስራዎችን በሚመለከት በቀጣይ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በሳሙኤል አባተ
ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *