ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ተጠቂዋ ከ አንድ ሚሊዮን በማለፍ ከአፍሪካ የመጀመርያዋ ሀገር ሆነች::

በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ 19 ተጠቂ ከ 1 ሚሊዮን ያለፈው አዲስ አይነት ዝርያ ያለው የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ መገኘቱ ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው፡፡
የተጠቂው ቁጥር መብዛት የሆስፒታሎችን ጥበትና የህክምና ቁሳቁሶችን እጥረት ማስከተሉ አልቀረም፡፡

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ይጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ትናንት እንደተገለፀው በደቡብ አፍሪካ 1 ሚሊዮን 4 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ 26 ሺህ 735 ያህሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡

501V2 የተባለው አዲሱ ኮሮና በምስራቅ የኬፕ ግዛት ከተገኘ በኋላ በሌሎቹ የሀገሪቱ ክፍሎች በፍጥነት እየተሰራጨ ነው፡፡
በዚሁ በዝግመት ከቀደመው ቫይረስ በመጣው አዲስ አይነት የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ፤እግሊዝ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረጉ ማንኛውንም ጉዞዎች መከልከሏን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሌላ አይነት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ደግሞ በእንግሊዝ መገኘቱ የሚታወስ ነው፡፡
ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ሞሮኮ 432 ሺህ 79 ዜጎቿ በቫይረሱ ተጠቅተው ሁለተኛ ስትሆን 7 ሺህ 240 ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል፡፡ ግብፅ ደግሞ 131 ሺህ 315 ተጠቂ በማስመዘገብ ከእህጉሩ በተጠቂ ብዛት ሶስተኛ ስትሆን 7 ሺህ 352 ሰዎች ሞተውባታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ አስራት
ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *