በኢትዮጵያ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በህዳር 19 እስከ ታህሳስ 19 ቀን ባሉት 30 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለት መቶ ሶስት ያህል ዜጎች ሂወታቸው አልፏል፡፡

እንደዚሁም ባለፉት 30 ቀናት ብቻ 12 ሺህ ስምት መቶ ሁለት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ መረጃ ያስረዳል።

በዚህም በኢትዮጵያ የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ቁጥራዊ መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡

ልክ እንደ ተጠቂዎች ቁጥርም በሀገራችን የሟቾች ቁጥርም በየቀኑ እየጨመረ ይገኛል፡፡

እንደ ወርልዶ ሜትር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ 122 ሺህ 864 ዜጎች በቫይረሱ ሲያዙ 1 ሺህ 909 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሂወታቸው እንዳለፈ ነው የሚጠቁመው፡፡

እስካሁን ድረስ ከ109 ሺኅ በላይ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አግግመዋል፡፡

በዘህም ኢትዮጵያ ከአለም በተጠቂዎች ቁጥር 68ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ከአፍሪካ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን ድረስ ከ81 ሚሊየን በላይ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊየን ዜጎች ደግሞ ሂወታቸው አልፋል፡፡

እንደዚሁም ከ57 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አግግመውል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.