በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 99 በመቶ የቱሪዝም እንቅስቃሴ መቆሙ ተገለጸ።

ፓርኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ በኮቪድ-19 እና በአገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት 99 በመቶ የቱሪስት ፍሰቱ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል ብሏል፡፡

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የህብረተሰብ እና ቱሪዝም ዘርፍ ሐላፊ አቶ ታደሰ ይግዛዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአገራችን ከገባ ጊዜ ጀምሮ ወደ ፓርኩ የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በአገሪቱ የሚታየዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ 99 በመቶ የቱሪስት ፍሰቱ እንደቆመ ታዉቋል፡፡

ፓርኩ ለአገሪቱ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ በአካባቢዉ የሚገኙ ዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንደነበሩ የተናገሩት ኃላፊዉ አሁን ላይ ግን ለችግር መዳረጋቸዉን አንስተዋል፡፡
በቱሪዝም ዘርፉ ተደራጅተዉ የሚገኙ 6 ማህበራት እንዲሁም የአስጎብኚና ድጋፍ ሰጪ አካላትም የችግሩ ሰላባ ሆነዋል ብለዋል፡፡

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ስድስት ወረዳዎችን እንደማዋሰኑ መጠን ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች በጎብኚዎች ማነስ ምክንያት ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አሁን ወቅቱ ከፍተኛ የጎብኚዎች ፍስት የሚስተናገድበት ወቅት የነበረ ቢሆንም ፓርኩን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ነዉ አቶ ታደሰ ያስታወቁት፡፡
ሁኔታዉ በቀጣዮቹ 2 ወራት በዚህ የሚቀጥል ከሆነም የቱሪዝም ዘርፉን ክፉኛ ይጎደዋል ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም መንግስት ፤አስጎብኚ ድርጅቶች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ትኩረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያለዉ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ የተረጋጋ እንደሆነና ጎብኚዎች መጥተዉ እንዲጎበኙ ሲሉ አቶ ታደሰ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በአባቱ መረቀ
ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *