ፌዴራሽኑ እንዳስታወቀው ከቀናት በፊት ተማሪ አብርሃም ዱሬሳ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ቤት ያገኘ ሲሆን ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር።
የመውጫ ፈተናውን ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሀሙስ በሰላም ተፈትኖ የመጨረሻው የፈተና ዕለት ማለትም አርብ የመፈተኛ ኮዱን ረስቶ ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ መሄዱን ፌደሬሽኑ ገልጿል።ካለ መፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ የመፈተኛ ኮዱን ይዞ ሲመጣ የመፈተኛ ሰዓት አልፏል ይባላል።
ፈተናው ከጠዋቱ 3፡30 የሚጀመር ሲሆን አብርሃም ግን አስር ደቂቃ ዘግይቶ 3፡40 ይደርሳል። ሱፐርቫይዘሩ መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ይሞክራል። ተማሪ አብርሃም_ዱሬሳም በተለያየ መንገድ ይማፀናል።
አይነ_ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም ፈተናውን እንዲወስድ ግን እንዳልተፈቀደለት ተገልጿል።ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ ። ሲበሳጭ ይውላል።
ምሽት ላይ ወደ ቤቱ በመግባትም ቤቱን ዘግቶ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ ከፍተኛ ቃጠሎ እንደደረሰበትና በኋላም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና ቢያገኝም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱ ማለፉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
በመሆኑም በተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ላይ የተፈጸመዉ ድርጊት ሰብአዊነት የጎደለዉ መሆኑን በመሆኑ መንግስት ክትትል አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ ፌዴሬሽኑ ጠይቋል።በኢትዮጵያ ከ17 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም











