እንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት ገበያና ከጉምሩክ ማህበር የሚያስወጣው የንግድ ስምምነት መተግበር ተጀመረ።

የብሬግዚት የመጨረሻው ንግድን የተመለከተው ድርድር ማለቁን ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል።
እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ስለተነጠለች ከህብረት ሀገራቱ በሚኖራት ንግድ፤ ምርቶቿ ላይ ታሪፍ ሊጫን ይችላል የሚለው ስጋት እንዳበቃለት ተገልጿል።

እንግሊዝን ከአውሮፓ ህብረት ነጠላ (የጋራ አንድ ገበያ) ገበያና ከጉምሩክ ማህበር የሚያስወጣው የንግድ ስምምነት ዛሬ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ከወሰነች በኋላ ፤ ከህብረቱ ጋር እንዴት ባለ መልኩ ነው ንግድ የምታከናውነው የሚለው ጉዳይ የተራዘመ ድርድር ተደርጎበታል፡፡

አውሮፓ ህብረትና እንግሊዝ የገና ዋዜማ ዕለት ከተስማሙ በኋላ፤ ትናንት የእንግሊዝ ፓርላማ በከፍተኛ ድምፅ ደግፎታል፡፡
እንግሊዝን ከአወሮፓ ህብረት ነጠላ ገበያ እና ከጉምሩክ ማህበር የሚያስወጣ ቢሆንም እቃዎች ላይ ታሪፍ ሊጫን ይችላል የሚለው ዕድል አብቅቶለታል፡፡

ዛሬ ህጉ ላይ ከሰፈረ በኋላ ስምምነቱ ተብባራዊ መሆን እንደሚጀምር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የፓርላማ አባላትን ካመሰገኑ በኋላ የዚህችን ታላቅ ሀገር ዕጣ ፈንታ አሁን ጠበቅ አድርገን በእጃችን ይዘነዋል ብለዋል፡፡
ተቃዋሚዎች ግን አሁንም እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት በመነጠሏ የከፋ ሁኔታ ነው የሚገጥማት እያሉ ነው፡፡

ይሄ ስምምነት በይፋ ተግባራዊ መሆን እስኪጀምር ፤ እንግሊዝ ህብረቱ በሚመራበት የብራስልሱ የንግድ ደንብ እየተመራች ትቀጥላለች፡፡

እንደ ሪዮተርስ ዘገባ ፤ የመጨረሻው የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት የመነጠያ ጊዜ (ብሬግዚት) ዛሬ እውን የሚሆነው ፤ ከህብረቱ ለመነጠል በህዝበ ውሳኔ ከመረጠች ከ 4 አመት ከ 6 ወር በኋላ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ አስራት
ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *