አብን፣ መኢአድ እና ባልደራስ ፓርቲዎች ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታወቁ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት( መኢአድ) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በቀጣዩ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ አዲስ አበባ ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታውቀዋል። የአብን ምክትል ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ የሱፍ ኢብራሒም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ሶስቱ ፓርቲዎች በጥምረት ሊሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ጥምረቱ በሶስቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች መካከል ውይይት ተደርጎ ስምምነቱ የመጨረሻ ምዕራፍ […]

ኢትዮጵያ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሎጂስቲክስ ማህበርን እንድትመራ ተመረጠች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ማህበሩን እንድትመራ መመረጧም ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኤግዚቢሽኖች ማእከል መዳረሻ እንደሚያደርጋት ተገልጿል። የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (EFSAA) መስራች ወ/ሮ ኤልሳቤት ጌታዩን እንዳሉት፣ ማህበራቸው የአለምአቀፉ የእቃ አስተላላፊዎች ማህበራት ፌዴሬሽን (FIATA) ብቸኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ወኪል መሆኑን ገልጸዋል። FIATA በስሩ ካሉት ክልሎች ውስት ኢትዮጵያ እንድትመራ የተደረገው የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የእቃ አስተላላፊ ኩባንያዎች ውስጥ መሆኑን አውስተዋል። […]

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 140 ሺህ ቶን ሰሊጥ ማገበያየቱን የኢትዮጲያ ምርት ገበያ አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ምርት ገበያው ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ከ19 ቢሊዮን በላይ ብር ማገበያየቱን ገልጿል። ምርት ገበያው በተያዘው የ2013 በጀት ዓመት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው። ምርት ገበያው ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 19 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 320 ሺህ ቶን ምርት ማገበያየቱን ገልጿል። ከተገበያዩ ምርቶች መካከልም ቡና፣ቦለቄ፣ሰሊጥ፣አኩሪ አተር እና ሌሎች ምርቶች እንደሆኑ በመግለጫው ተገልጿል። […]

በኢትዮጵያ ካሉ 70 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴት ከፍተኛ አመራሮች ያሏቸው ፓርቲዎች ሁለት ብቻ እንደሆኑ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስርዓተ-ፆታ አካታችነት ኦዲትን ሀገራዊ ጥናቱን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጥናት መሰረት አንድ ሴት መሪ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ተፎካካሪ ፓርቲ ሲሆን መሪዋም ወ/ሮ ቆንጂት ብርሃን መሆናቸው ተገልጿል። ሁለተኛዋ ምክትል መሪ ደግሞ ከአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ተፎካካሪ ፓርቲ ሲሆን ወ/ሮ ማርታ ካሳ መሆናቸው ታውቋል። […]

ጆዜ እንደ ልማዳቸው ክሎፕን ወርፈዋል::

Posted Leave a commentPosted in ስፖርት

ጆዜ ሞውሪንሆ የጨዋታ ዳኞች እና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰዎች አንዳንድ አሰልጣኞች በተጠባባቂ ወንበር ጫፍ ላይ የሚፈጽሙትን ያልተገባ ድርጊት በቸልታ እያለፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ክሎፕ በቅርቡ ከበርንሌይ አሰልጣኝ ሾን ዳይች ጋር ወደ መልበሻ ክፍል በሚወስደው መሿለኪያ መጋጨታቸውን ለአብነት ይጠቅሳሉ፡፡ የቶተንሃሙ አሰልጣኝ እንደ የርገን ክሎፕ ዓይነት የተቀናቃኝ ቡድን አሰልጣኞች እርሳቸውን ለእገዳ እና የገንዘብ መቀጮ ሲያስጥሉባቸው የነበሩ ድርጊቶችን እየፈጸሙ ያለ […]

ኢትዮጵያ የቀጣይ አስር አመት የትራንስፖርት መሪ እቅዷን ለማሳካት ከ3 ትሪሊየን ብር በላይ ያስፈልጋታል ተባለ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የትራንስፖርት ዘረፍ የአስር አመት መሪ የልማት እቅዱን ለማሳካት 3 ነጥብ 04 ትሪሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 69 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር በዘርፉ ከሚሰጠው አገልግሎቶች በሚሰበሰበው ገቢዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡ የተቀረው ደግሞ ከመንግስት በጀት ከብድር እና ከውጪ ከሚገኝ እርዳታ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ዘርፍ የአስር አመት መሪ የልማት እቅድ […]

ከ139 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እንዳለዉ፣በ20/80 የቤቶች ልማት ፕሮግራም 100 ሽህ 768 ቤቶችና በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም 38 ሽህ 240 ቤቶች በድምሩ 139 ሽህ 8 ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ይህን ያለዉ የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነዉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም 69 ነጥብ 39 ሄክታር መሬት በመረከብ 25 ሽህ 946 ቤቶችን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እያደረኩ ነዉ ብሏል፡፡ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጤና ሚኒስቴር ሥር የሚገኘውን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጤና ሚኒስቴር ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘውን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅት በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች አካላቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያን የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ በማምረት የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡ ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይሄንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ወገኖች […]

የስምንት ዓመቱ ታዳጊ ከናይኪ ጋር ተፈራረመ::

Posted Leave a commentPosted in ስፖርት

ሜሲ ከናይኪ ጋር የመጀመሪያ ኮንትራቱን የተፈራረመው በ15 ዓመቱ ነበር፡፡ ኔይማር ደግሞ በ13 ዓመቱ፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ከሚከሰቱ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ የስምንት ዓመቱ ካዋን ባሲል ከናይኪ ጋር የመፈራረም ዕድል ያገኘው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ በቀላሉ ተሰጥኦን ማሳየት የሚቻልበት ጊዜ ላይ በማደጉ ከኔይማር እና ሊዮኔል ሜሲ ባነሰ ዕድሜ ዕድሉን ያገኘው ለዚያ ነው፡፡ ገና በለጋ ዕድሜው የብራዚል እግር ኳስ […]

በአዲስ አበባ ድንገት በተከሰተ የእሳት አደጋ የ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል፡፡ አደጋው የደረሰው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቦኖ ውሃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ በቀበሌ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው፡፡ በተከሰተው ድንገትኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ታውቋል፡፡ ህይወታቸው ያለፈው አንድ አረጋውያንና አንድ […]