ኢትዮጵያ በ5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ ብሔራዊ ማይክሮ አልጌ ባዮቴክኖሎጂ ቤተ ሙከራ ገነባች።

የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የብሄራዊ ማይክሮ አልጌ ቤተ ሙከራ አስመርቋል፡፡

ማይክሮ አልጌ በኢትዮጵያ በስፋት የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ይከላከላል ተብሏል፡፡

ማይክሮ አልጌ ለሰው ልጅ እጅግ ጠቃሚ መሆኗ የተረጋገጠ ነው የሚሉት ዶክተር ሀብቴ ጀቤሳ የማይክሮ አልጌ ዘርን በማልማት በሀገሪቱ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ለመከላከል ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል

ቤተ ሙከራው የህጻናት አልሚ ምግቦችን ለማምረት የሚረዳ የማይክሮ አልጌን ዘር ለማውጣት ያስችላል ተብሏል፡፡

የማይክሮ አልጌ ዘር በቢሾፍቱ አብያታና ሻላ ሀይቆች ላይ በስፋት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን በእነዚህ አካባቢዎች ንጽህናው በተጠበቀ መልኩ ማምረት ይቻላል ሲሉም ዶክተር ሀብቴ ተናግረዋል

በአሁኑ ወቅት በኢንስቲትዩቱ በዘርፉ 5 ተመራማሪዎች ያሉ ሲሆን ወጣት ባለሙያዎችን ለማፍራትም ስልጠና እንደሚሰጥ ሰምተናል።

5 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎ የተገነባው ቤተ ሙከራ በየ15ቀኑ 100 ሊትር ዘር የሚያመርት ሲሆን ወደ ገበያ የሚያወጣ ኢንቨስተር ግን አሁንም አላገኘንም ብለዋል ዶክተር ሀብቴ

ማይክሮ አልጌ የስኳር ህመም የኩላሊት ጠጠር የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች ቢመገቡት ለጤናቸው መልካም ለውጥን ያዩበታል ሲል ምክራቸውን ለግሰዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.