የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ16 ሰዓታት ውሃ እንደሚያቀርብ አስታወቀ።

በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የውሃ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ንጉሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከሆነ በበዓል ሰሞን ከፍተኛ የሆነ የውሃ ፍጆታ ስለሚኖር ሙሉ በሙሉ ሳይቋረጥ ማድረስ ቢከብድም ለ10 ሰዓታት ያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ወደ 16 ሰዓት ከፍ እንዲል በማድረግ ተጠቃሚነታቸው ሊጨምር ይችላል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሲልም ሆነ በአሁኑ ወቅት እንደሚስተዋለው የመብራት ሃይል መቆራረጥ ስራቸዉን ከባድ ሲያድርገው እንደነበረ ገልወጸዉ፣ አሁንም ለዚህ መፍትሄ ካልተገኘ ችግሩ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በረድዔት ገበየሁ
ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *