በአልነጃሺ መስጅድ ላይ ጥቃት የፈጸሙት አካላትን ከህግ ፊት እንዲቀርቡ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠየቀ።

ምክር ቤቱ በታላቁ የነጃሺ ታሪካዊ መካነ ቅርስ መስጂድ ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ የሆኑት ሸህ ቃሲም ሙሓመድ ታጁዲን በመግለጫቸው እንዳሉት፣ የአለም ቅርስ በሆነው የነጃሺ ታሪካዊ መስጂድና የቀብር ቦታ ላይ በከባድ ጦር መሳሪያ ጉዳት ከመድረሱ በተጨማሪ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የተለያዩ የመገልገያ ቁሳቁሶች ተዘርፈዋል ብለዋል።

ሼህ ቃሲም ታላቁ የኢትዮጵያ ንጉስ ማስመሃት ወይም ነጃሺ ከዛሬ 1400 አመታት በፊት አለም እንደዛሬው ፣
የስደተኞች መብትን በማያከብርበት ዘመን መብቶችን ያከበረ፣
ከዘመኑ ቀድሞ ባልተለመደ ሁኔታ ከነብዩ ሙሃመድ (ሰ.ዓ.ወ) ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ስደተኞችን ከመንግስት ልኡካን ጋር ተከራክሮ በሰላም የተቀበለና ያስተናገደ፣
እንደዛሬው የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት በህገ መንግስት ባልተረጋገጠበት፣ ሺህ ዘመናትን ቀድሞ ሰወች የፈለጉትን እምነት የመከተል ነፃነትን ያወጀ፣ በዚህ ተግባሩም አለም በሙሉ በአድናቆት ሲያወሳው የሚኖር የሃበሻ ንጉስ መሆኑን አውስተዋል።

የዚሁ ታላቅ ንጉስና የነብዩ ሙሓመድ (ሰ.ዓ.ወ) ባልደረባዎች መቃብርና በስሙ የተሰየሙ በአላም ከሚገኙ ትቂት ቀደምት መስጂዶች አንዱና ታሪካዊ ቦታ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሰይሆን የመላው አለም ቅርስ እንደሆነ ነው የገለፁት።

ስለሆነም በዚሁ ቅርስ ላይ በደረሰው ጥቃት ጠ/ምክርቤታችን የተሰማውን ልባዊ ሃዝን ይገለጻል ብለዋል ሸህ ቃሲም።

ጠ/ምክርቤታችንም ይህንን ፍፁም ፀያፍና አሳፋሪ የወንጀል ድርጊት በፅኑ ያወግዛል ብለዋል።

ሸህ ቃሲም ቅርሱ የደርስበትን ትክክለኛ ጉዳቱንና የጉዳቱን መጠን የሚያጣራ ቡድን ወደ ቦታው ተልኳል ብለዋል።

ቡድኑም በአጭር ጊዜ ሪፖርቱን እንዲያቀርብ ለማድረግ ጠ/ምክርቤቱ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም መንግስተና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ይህንን አስነዋሪ ድርጊት የፈፀሙትን አካላት በአፋጣኝ ለፍትህ እንዲቀርቡ እንዲያርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በጅብሪል ሙሀመድ
ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *