ቻይና ከአለም የጤና ድርጅት የተላኩትን የመርማሪ ቡድን አባላት ቪዛ መከልከሏ ድርጅቱን አስቆጥቷል፡፡

ቻይና የዓለም ጤና ድርጅት ለላካቸው የመርማሪ ሳይንቲስቶች ቡድን ቪዛ መከልከሏ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ጋር በተያያዘ የዓለም ጤና ድርጅት አንድ የመርማሪዎች ቡድን ወደ ቻይና ለመላክ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ባለፈው አንድ ወር ግድም ነበር ያሳወቀው፡፡

ይህ የመርማሪዎች ቡድን የኮሮና ቫይረስ መነሻ ነች በምትባለው ዉሃን ከተማ በመገኘት የቫይረሱን መነሻ ትክክለኛ ነገር ለማወቅ ነበር ወደ ስፍራው ለማቅናት ያሰበው፡፡

ይህ ቫይረስ ተገኘ የተባለው በ 2019 መጨረሻ አካባቢ ሲሆን መነሻውም ቻይና ውስጥ የሚገኝ የእንሰሳት መሸጫ ገበያ ውስጥ መሆኑ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ለረዥም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ይህ አጣሪ ቡድን ወደ ቻይና የማምራት ጉዳይ ላይ ስምምነት የተደረሰው ባለፈው ታኅሣስ ነበር።

እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ የዓለም ጤና ድርጅት ከቻይና ጋር ረዥም ድርድር ማድረጉ ታውቋል።

ቻይና በተደጋጋሚ ይህንን ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ላለመቀበል ስታንገራግር ቁይታለች፡፡ እናም አሁን ደግሞ ምክንያቱ ባይገለጽም የመግቢያ ቪዛ አላዘጋጀችም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚህም ሰበብ ከመርማሪ ቡድኑ ሁለቱ የጀመሩትን ጉዞ አቋርጠው መመለሳቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡
እንዲሁም ሌላኛውም ሶስተኛውም ቢሆን በሶስተኛ ሀገር ትራንዚት በማድረግ ላይ እያለ ጉዳዮን እንደሰማ ተነግሯል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት መርማሪ ቡድኑ ቻይና መግባት ያልቻለው ከቪዛ ጉዳይ በተያያዘ ስለመሆኑ የአለም የጤና ድርጅት ተናግሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔ አበባ ሻምበል
ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *