በኢትዮጵያ፤ በማሌዥያና በሌሎችም ቦታዎች ላይ አውሮፕላኖች እንዲከሰከሱ ምክንያት የነበሩትን ዲዛይኖች ደብቋል በሚል ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በንዘብ ሊቀጣ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ቦይንግ አውሮፕላን ኩባንያ በተለያዩ የአለም አካባቢዎች ከተከሰከሱት 737 ማክስ አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ የአውሮፕላኖችን የዲዛይን መረጃ በመደበቁ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዘገባው እንደሚለው ከሆነ፤ ከግልፅነት ይልቅ ትርፍን አስበልጧል ሲል ቦይንግን የከሰሰው የአሜሪካ ፍትህ መስሪያ ቤት በአውሮፕላኖች ላይ ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር እንዳይደረግባቸው ከልክለው ነበር ብሏቸዋል፡፡

በዚህም የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ዋናው ምክንያት እንደነር መስሪያ ቤቱ መግለጹን መረጃው አመላክቷል፡፡

ከ2.5 ቢሊየን ዶላሩ መካከል 500 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋዎች ህይወታቸውን ላጡ መንገደኛ ቤተሰቦች የሚከፈል ካሳ ነው ተብሏል።

1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ለቦይንግ ኩባንያ አየር መንገዶች የሚከፈል መሆኑንም ቢቢሲ በዘገባው ላይ ገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሀመድ
ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *