ቻይና አሜሪካን በውስጣዊ ጉዳዮቿ ብቻ ወደ ውድቀት እያመራች አንደሆነች ገለፀች፡፡

ከደቂቃዎች ቀደም ብሎ የቻይና ሚዲያ እንዳስታወቀው፤ አሜሪካ በትራምፕ የስልጣን መውጫ አካባቢ ወደ እርስበርስ ግጭትና ብጥብጥ እያመራች እንደሆነ ነው ያስታወቀው፡፡

ሚዲያው እንዳለው ከሆነ፤ ያሳለፍነው ረቡእ በአሜሪካ ዋና ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች፤ ስድብና ዛቻ የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ እንደነበርም ጠቁሟል ሲል አልጃዚራ ዘግቦታል፡፡

ስለሆነም አሜሪካ አሁን ላይ የአመራር፤ የአስተዳደርና የዲሞራሲዊ አሰራር ግድፈት የሚታይባት ሀገር ሆናለች ሲል መረጃው ያትታል፡፡
ይህም ቻይና አሜሪካ ወደ ውስጣዊ መከፋፈልና መፈራረስ እንድትገባ ምልከት ነው ማለቷን ነው መረጃው የጠቆመው፡፡

ዎርልድ ታይምስ በበኩሉ የቻይናው ኮሚነስት ፓርቲ ተናገረ ብሎ እንደዘገበው ከሆነ ‹‹አሁን ላይ በአሜሪካ እንደነዚህ ያሉ አመጾች ሀገሪቷን ወደ ለየለት የርሰበርስ አለመተማመን፤ ብጥብጥና መከፋፈል ውስጥ አስገብቷታል ሲል ዘግቦታል፡፡

ለዚህ ደግሞ አሜሪካውያን ፖለቲከኞች በዲሚክራሲ ስም ህዝቡን ማታለላቸው ነው ይላል፡፡
ኮሙኒስት ፓርቲው አሜሪካ አሁን ከገባችበት ውጥረት ደግሞ እንዲህ በከላሉ መውጣትም አትችልም›› ሲል አክሏል፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *