በምዕራብ ወለጋ ዞን 8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መግደሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ 8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

በሕግ ማስከበር ስራው 6 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና 87 ደጋፊዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮሚሽኑ አክሏል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ወራት በዞኑ በተደረገው የሕግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ 265 የኦነግ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ገልጿል።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ ሲጠቀሙበት የነበረው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.