ኡጋንዳ በምርጫ ጣበያ ውስጥ ካሜራ ያለመጠቀም ህግ አወጣች፡፡

የኡጋንዳ ምርጫ ኮሚሽን በምርጫ ጣበያ ውስጥ ማንም ሰው ካሜራ እንዳይጠቀም ህግ ማውጣቷን አስታወቀች፡፡

መራጭ ወደ ድምጽ መስጫ ጣበያ ሲገባ በድብቅ ምርጫው እንዲያከናውን በማሰብ ነው ህጉ የወጣው ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ ምርጫ በሚደረግባቸው ቦታዎች አንድም ካሜራ እንዳይኖር የከለከለች ሲሆን በሞባይልም ሆነ በማንኛውም መሳርያ የትኛውም ቅጂ እንዳይከናወን ከልክላለች፡፡

እንዲሁም የትኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ተወዳዳሪ ምርጫ በሚያደርግበት ጊዜ ፎቶ መነሳት እና ማንሳትም ክልክል መሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሀገሪቷ ከ4 ቀናት በኃላ በምታደረግው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ማንም ሰው በወጣው ህግ መሰረት ወደ ምርጫ ጣበያ ስልክ ይዞ መግባት አይችልም፡፡

ኡጋንዳ የፊታችን አርብ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረች ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡

በዚህ ምርጫ ሀገሪቷን ለ30 አመታት የመሯት ዩዌሪ ሞሶቪኒ ዳግም በምርጫው ይሳተፋሉ፡፡

ከፕሬዝዳነቱ በተጨማሪም 11 ያህል ተፎካካሪዎች በምርጫው እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ ምርጫ ታዋቂው የሙዚቃ ሰው ቦቢ ዋይን የዩዌሪ ሞሶቪኒ ዋነኛ ተቀናቃኝ ይሆናል ተብሎ ተጠብቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.