ትዊተር የ70 ሺህ ሰዎችን አካውንት መዝጋቱን ገለጸ::

ትዊተር ይህንን ያለው ያሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ የዶንልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ደረጉትን አድማ ተከተሎ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

አመጹ እንዲደረግም ትዊተርን ተጠቅመው እንደነበርም አስታውቋል፡፡

ዶልድ ትራምፕ እራሳቸው ደጋፊዎቻቸውን አድማ እንዲያደርጉና አመጽ እንዲያስነሱም ትዊተራቻውን እንደተጠቀሙም ጠቁሟል፡፡

ከቀናት በፊት የዶናልድ ትራምፕ የትዊተር አኮውንታቸውን እንዳገደባቸው ያስታወቀው ትዊተር፤ አሁን ደግሞ ከዶንልድ ትራምፕ ደጋፊዎችን እና ጃንዋሪ 6 በዲሲ ከተማ በተደረገው አመጽ እጃቻው አለበት ያላቸውን የ70 ሺህ ሰዎችን አካውንት ማገዱን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቦታል፡፡

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *