የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ደቡብ ሱዳን ጁባ አቀኑ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር ማያርዲትና ሃይለማርያም ደሳለኝ በጁባ መምከራቸዉ ተሰምቷል፡፡፡

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር ማያርዲትና የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱን ሀገራት በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በዉይይታቸዉም አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተረጋጋ ሰላም መስፈኑን አስረድተዋል፡፡

ከዉይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የደቡብ ሱዳን የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቤትሪስ ካምሳ እንዳሉት፣ ሃገራቸዉ ሰላምን በማረጋገጥ ወደ ፊቷን ማዞሯንና ከኢትዮጵያ ጋርም ትብብሯን የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ወሳኝ መሆናቸዉን ነዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የተናገሩት፡፡

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ በንግድ፣በኢንቨስትመንትና በመሰረተ ልማት እንዲተሳሰር እያደረጉት ያለዉ እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነዉ ብለዉታል፡፡

አቶ ሃይለማርያም ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር አረጋግጠዉላቸዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሃይለማርያም በደቡብ ሱዳን የተረጋጋ ሰላም እንዲፈጠር ፕሬዝዳንት ቫልቫኪር የሰሩት ስራ የሚደነቅ መሆኑንም ጨምረዉ መናገራቸዉን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *