የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሆኑ ተገለጸ።

የኮቪድ_19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ”እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ” ንቅናቄ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
በአዲሰ አበባ ብሎም በመላው ሃገሪቱ የሚታየውን የቸልተኝነት ለመቆጣጠር ሲባል ንቅናቄው የተጀመረበት ዋነኛው አላማ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ125 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 ተይዘዋል።
ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

በኮሮና ሻይረስ ከታያዙት መካከል 57 ከመቶ የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ሲሆን ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ 70 በመቶ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሆኑ ተገልጿል።

ንቅንዌውን ያስጀመሩት በአዲስ አበባ ከተማ በምክተል ከንቲባ ማእርግ አቶ ዣንጥራር አባይ ባስተላለፉት መልእክት፣ አሁን የምንጀምረው ንቅንቄ ጥረታችንን የማጠናከር እና የሁላችንም ማህበራዊና ግላዊ ተሳትፎን የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

ንቅናቄው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረው፣ ሀገራችንንም ወደፊት እንድትራመድ ያደርጋታል ብለዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በሀገራችን አሁን ላይ የኮሮና ቫይርስ ወረርሽኝ አስፈሪ ደረጃ ላይ መድርሱን ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ አንድና ሁለት ሰዎች ተያዙ ብለን ስናዎራ ነበር፣ አሁን ግን በየቀኑ 4 መቶ ና 5 መቶ ሰዎች ተያዙ ብለን እያወራን እንገኛለን ብለዋል።

ይህም በቫይረሱ ዙሪያ ያለንን ቸልተኝነት ያመለክታል ብለዋል።
በመሆኑም ንቅናቄው የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋረ ተሳተፎ ማድረግ ግድ መሆኑን ነው ያሳሰቡት።

ሚኒስትሯ አያይዘውም በአሁኑ ሰአት በመዲናችን በአዲስ አበበ የማስክ ተጠቃሚዎች ከ54 በመቶ በታች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት የማስክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም ከቀን ወደ ቀን ግን እያሽቆለቆለ እንደመጣ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *