የማላዊ ሁለት ሚኒስትሮች በኮቪድ 19 ህይታቸው አለፈ::

ቢቢሲ እንደዘገበው ትናንት በኮቪድ 19 ህይወታቸው ያለፈ ሁለተኛው የማላዊ የካቢኔ ሚኒስትር ሆነዋል የትራንስፖርት ሚኒስትር ሲዲክ ሚያ፡፡

የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሊንግሰን ቤሌካንያማ ደግሞ ሁለት ሰአት ቀደም ብለው ነው ህይወታቸው እንዳለፈ የመረጃ ሚኒስትሩ ያረጋገጡት፡፡
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛረስ ቸክዌራ በሬዲዮ ለህዝቡ ኮስተር ያለ ማሳሰብያ አስተላልፈው ነበር፡፡

ኮቪድ 19 ለመከላል መወሰድ ያለባችሁን ጥንቃቄ ሁሉ ተግብሩ ፣ የተጠቂውና የሟች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ብለው ነበር፡፡
የፕሬዝዳንቱ ቢሮ በሚኒስትሮቹ ሞት የ 3 ቀን ሀዘን እንደታወጀ ገልጿል፡፡

በሔኖክ አስራት
ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *