3 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ከብት አርቢዎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ለመግባት መሞከራቸው ተገለጸ።

የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በክልሉ ስር በምትገኘው ኢታንግ ልዩ ወረዳ በምትዋሰንበት ደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ከብት አርቢዎች ከነከብቶቻው ከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ወደ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ለመግባት ሲሞክሩ በፀጥታ ልዩ ሃይሎች ክትትል እንዳይቡ ማድረግ መቻሉ ተነግሯል፡፡

የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ኦቶ ኦኮት ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት እነዚህ የደብብ ሱዳን የከብት አርቢዎች አሁንም ቢሆን በድንበር በኩል ወደ ኢታንግ ወረዳ ለመግባት ጥረት እያደጉ ነው፡፡

በዚህ አጎራባች ድንበር አማካኝነት በተደጋጋሚ የደቡብ ሱዳን ከብት አርቢዎች በህገ ወጥ መንገድ በመግባት ከብቶቻቸውን ለግጦሽ እንደሚያሰማሩ የነገሩን አቶ ኦቶው በአሁነኑ ሰዓትም ከ 3 ሺ የሚልቁ ከብት አርቢዎች እጅግ የበዙ የቀንድ ከብቶችን ወደ ክልሉ በማስገባት ለግጦሽ ማሰማራት መፈለጋቸውን ነግረውናል፡፡

ይሁን እና እነዚህ የቀንድ ከብቶች ወደ ክልሉ በመግባታቸው አንድም በወረዳው የሚገኘውን ሃብት ከማባከን ባሻገር የተለያዩ በሽታዎችን ይዘው የሚመጡበት አጋጣሚ መኖሩን ነግረውናል፡፡

ከዚህ ባሻገርም በከብት ማርባት የተሰማሩት እኚሁ የደቡብ ሱዳን ከብት አርቢዎች ህገ ወጥ የጦ መሳሪያ በማዘዋዋር ህገ ወጥ ድርጊት እንደሚፈፅሙ ስለሚታወቅ አሁንም ቢሆን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን ነግረውናል፡፡

የኢታንግ ልዩ ወረዳ ዋንኬ እና ሜራ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች ከደቡብ ሱዳን ጋር ትዋሰናለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *