የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የግድያና አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆኑን የሲቪል ማህበራት ገለጹ፡፡

ማህበራቱ እንዳሉት፣በክልሉ ንጹሃን ሴቶች እየተገደሉ፣የአስገድዶ መድፈር እየተፈጸመባቸዉና ንብረታቸዉም እየተዘረፉ ነዉ ብለዋል፡፡

ማህበራቱ ይህን የገለፁት በግጭት ምክንያት ህይዎታቸውን፣ ክብራቸውን፣ ንብረታቸውን እና ማህበራዊ አግልግሎታቸውን ላጡ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሰ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምፅ እንሁንላቸው የሚል መግለጫ በጋራ በሰጡበት ወቅት ነው።

ማህበራቱ በሃገራችን በትግራይ ክልል፣ በመተከል፣ በጉራፈርዳ፣ በሲዳማ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በሌሎችም የሀገራችን ክፍሎች የደረሱትን የሰብኣዊ ጥቃቶችን አውግዘዋል።

በግጭቱ በተለይ ለአዳጋ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ ህፃናትና አረጋውያን ደግሞ በከፋ ሁኔታ ተጎድተዋል፣ ከግጭቱ የተረፉትም ቢሆኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

የሲቪል ማሀበራቱ መንግስት ዜጎች የሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲጠበቅ እንዲሰራም አሳስበዋል።በግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ፣አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣ የህክምናና ሌሎችንም የቁሳቁስ ድጋፍና በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ሰዎችም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ነው ያሳሰቡት።

በትግራይ ክልል ጉዳዩ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን የነበረው መሆኑን የገለጹት ማህበራቱ፣ በሌሎች የነበሩት ግን ትኩረት አላገኙም ብለዋል።

በሃገር ዉስጥም ይሁን በውጪ ያሉ መንግስታዊና መንግስታ ያልሆኑ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም ቢሆኑ፣ በነበሩት ግጭቶች ጉዳት ለገጠማቸው ወገኖቻችን እንዲያገግሙ የሚያስችል የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *