በገጠር የኢትዮጵያ አካባቢዎች መብራትን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት የህዝቡ ተበታትኖ መስፈር ፈተና መሆኑን ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ።

በገጠር ሀይልን ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት የህዝቡ የተበታተነ አሰፋፈር ትልቅ ፈተና ሆኗል ሲሉ የውሀ ኢነርጂና መስኖ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት የገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ነው፡፡

80 በመቶ የሚሆነው በግብርና የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል አብዛኛው የኤሌክትሪክ አገልግሎት አያገኝም።

በዚህም ለምግብ ማብሰያ ለውሀ ማሚቂያ ሀይል የሚያገኘው ከማገዶ እንጨት ከከሰልና ከመሰል የደንና ግብርና ተረፈ ምርቶች እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ሀይልን ለማዳረስም የተለየ አቀራረብ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ይህንን ስራም ከ1960ዎቹ ጀምሮ በተበታተነ መልኩ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ከ1991 ጀምሮ ግን የኢትዮጵያ የገጠር ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ሲሰራው እንደነበር ተነግሯል፡፡

ማዕከሉ የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም ሲሆን ከኤሌክትሪክ መስመር ውጪ የሆኑ የሀገሪቱ ህዝቦችን ታዳሽ የኢነርጂ ምንጭ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንዳለም ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.