38 ኩንታል ካናቢስ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ዛሬ ከሌሊቱ 7 ሰአት ላይ መነሻውን ሻሸመኔ ያደረገው ኮድ 3 አዲስ አበባ 33498 አይሲዙ መኪና በአቃቂ ቃሊቲ ቱሉዲምቱ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ 38 ማዳበሪያ ካናቢስ መያዙን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጽህፈት ቤቱ ሰምቷል፡፡

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሮክ ቅንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሀላፊ አቶ ዋሪዮ ጉዮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ዕፁን ሲያጓጉዙ የነበሩ ሾፌርና ረዳት ጨምሮ ስራውን በውክልና ይሰራል የተባለ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

አቶ ዋሪዮ እንዳሉት የካናቢሱ መጠን ለማወቅ በዚህ ሰአት እየተመዘነ ይገኛል በግምት ግን ከ3ሺህ ኪሎ በላይ ነው ብለዋል፡፡

በያይኔ አበባ ሻምበል
ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.