በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የተሳተፈ የውጭ ሀይል አለመኖሩን አምባሳደር ዲና ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ እና የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ የተለያዩ መሆናቸውንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አምባሳደሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ግድቡን በተመለከተ ሱዳኖች ወጣ ገባ አቋም የሚያሳዩቱ በሶስተኛ አካል ምክንያት ነው።

የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ህዝብ ትልቅ ጥቅም እንደሚያስገኝ ሱዳናዊያን ምሁራን የሚያውቁት ጉዳይ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የህዳሴ ግድብና የኢትዮ-ሱዳን ድንብር ጉዳይ ግኙነት የሌላቸው እና በተናጠል የሚታዩ ጉዳዮች እንደሆኑ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

አምባሳደሩ አክለውም የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ገብቶ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ ነው መባሉ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል።

“በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ማንም የውጭ ሀይል አልተሳተፈም በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራን የተተኮሰው ሮኬት ቀጠናዊ ለማደረግ ነበር ነገር ግን ይህ አልተከሰተም” ሲሉም አምባሳደሩ አክለዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳን መሪዎች እኛ ወደ ሰሜን ህግ የማስከበር ስራ ላይ በመሆናችን የእናተን መግቢያ ድንበሮች ጠብቁ ነው ያሉት ብለዋል አምባሳደር ዲና።

ሱዳንን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ሰራታለች ፣ በሁለቱ ሀገራት የከፍ የነቆራ ታሪክ የለም ሲሉም አክለዋል አምባሳደሩ።

በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን ብለዋል አምሳደር ዲና።

በዳንኤል መላኩ
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *