የአፍሪካ መሪዎች የዘንድሮውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ ላይመጡ ይችላሉ ተባለ።

የአፍሪካ ህብረት መሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እና በተመረጡ ሌሎች ከተሞች ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤውን ያካሂዳል።

በአሁን ሰዓትም የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች ዓመታዊ ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ሕብረቱ ዓመቱን “የባህል፤ኪነ ጥበብ እና ቅርስ ጥበቃ ለምንፈልጋት አፍሪካ” በሚል ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከህብረቱ ኮሙንኬሽን የስራ ክፍል እንደሰማው ከሆነ የዘንድሮው የ2021 ዓመት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ያለበት ቢሆንም መሪዎቹ በአካል ወደ አዲስ አበባ ላይመጡ ይችላሉ።

የኮሮና ቫይረስ ደግሞ መሪዎቹ ወደ ሕብረቱ መዲና አዲስ አበባ በአካል እንዳይመጡ ምክንያት መሆኑን ሰምተናል።

ይሁንና እስካሁን ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በገጽ ለገጽ ወይስ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ይካሄድ? የሚለው ጉዳይ አለመወሰኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄዱ የቪዲዮ ውይይቶች ላይ ጉዳዩ ውሳኔ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ከቀናት በፊት ወደ ተግባር የተቀየረው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና፣ሽብርተኝነት፣ኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ መሪዎቹ የሚወያዩባቸው አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

በሳሙኤል አባተ
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *