የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጠ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አምባሳደር ዲናበዚህ ጊዜ እንዳሉት “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳን መሪዎች እኛ ወደ ሰሜን ህግ የማስከበር ስራ ላይ በመሆናችን የእናተን መግቢያ ድንበሮች ጠብቁ ነው ያሉት ብለዋል አምባሳደር ዲና።

ሰዳንን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ሰርታለች ፣ በሁለቱ ሀገራት የከፋ የነቆራ ታሪክ የለም ሲሉም አክለዋል አምባሳደሩ።

በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን ብለዋል አምሳደር ዲና።

በዳንኤል መላኩ
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.