ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ሲሰናበቱ ጆ ባይደን ደግሞ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ገብተዋል፡፡

ሀገረ አሜሪካንን ላለፉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለተተኪው ፕሬዝዳን ጆ ባይደን ለቀው ወጥተዋል፡፡

ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የተመረጡት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ በዛሬው እለት በይፋ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

በበዓለ ሲመታቸው ላይ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ሁሴን ኦባማ፣ ቢል ክሊንተን እንዲሁም ጆርጅ ደበሊው ቡሽ ሲገኙ ዶናልድ ትራምፕ አሻፈረኝ ብለው አልተገኙም፡፡
በዝግጅቱም 25 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች የዋሽንግተን አደባባይን ከነውጠኛ የትራምፕ ደጋፊዎች በተጠናከረ ሁኔታ ሲጠብቁ የታዩ ሲሆን በዓለ ሲመቱን ሊዴ ጋጋ አድምቃዋለች፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.