በእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ የሚሳተፉት ቼልተን ታወን እና ኒውፖርት ካውንቲ 1ለ1 በተለያዩበት ጨዋታ የኒውፖርት ካውንቲው ግብ ጠባቂ ቶም ኪንግ የተጫዋችነት ዘመኑን የመጀመሪያ ጎል አስቆጥሯል፡፡
የ25 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ከራሱ የፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ የመታት ኳስ በንፋስ ታግዛ በተጋጣሚያቸውን ቼልተንሃም ግብጠባቂ ጆሽ ግሪፊዝ ፊት ነጥራ ጎል ሆናለች፡፡
በእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ለመጨረሻ ጊዜ ጎል ያስቆጠረው ግብ ጠባቂ የሞርካምቡ ባሪ ሮች ነው፡፡ በየካቲት 2016 ፖርትስመዝን በገጠሙበት ጨዋታ ፡፡
ጎሏን ያስቆጠረው ግብ ጠባቂ ኪንግ ከራዲዮ ፋይቭ ጋር ባደረገው ቆይታ
‹‹በፕሮፌሽናል ሊግ ያስቆጠርኩት የመጀመሪያ ጎል ነው፡፡ ‹‹ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ደስታዬን እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ እንኳን አላወቅኩም፡፡
ከጨዋታው በኋላ ግብ ጠባቂውን ይቅርታ ጠይቄዋለሁ፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ሞርካምብን በገጠምንበት ጨዋታ እኔም ተመሳሳይ ጎል ለጥቂት ተቆጥሮብኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡
እንደዚህ ዓይነት ጎል ማስተናገድ ደስ የሚል ስሜት እንደማይፈጥር አውቀዋለሁ፡፡››
በአቤል ጀቤሳ
ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም











