ቻይና በ28 የአሜሪካ ሰዎች ላይ ማእቀብ ጣለች፡፡

ቻይና ማይክ ፖምፒዮን ጨምሮ በ28 በቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣኖች ላይ ማእቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

ሀገሪቷ በቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣኖች ላይ ማእቀቡን የጣለችው በቻይኛ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል።

ማእቀቡ ከተጣለባቸው የቀድሞ ባለስልጣናት መካከል የትራምፕ የንግድ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ፒተር ናቫሮ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሮበርት ኦብሪን በተባበሩት ምንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ተወካይ ኬሊ ክራፍት እና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኙበታል፡፡

ቻይና ማእቀብ ከጣለችባቸው ጉሙቱ ሰዎች ውስጥም በትራምፕ አስተዳደር ተሰላችተው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን ለቀው የነበሩት የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የነበሩት ጆን ቦልተን እና አማካሪያቸው ስቴፈን ባነን ይገኙበታል፡፡

ቻይና እንደምትለው እነዚህ ሰዎች ትምክተኛ እና እራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች ናቸው በተለያዩ ጊዜያቶች የቻይናን ሉአላዊነት ሲጋፉ ቆይተዋልም ብላለች፡፡

በመሆኑም እነዚህ ባለስልጣናት ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ወደ ቻይና ሆንግ ኮንግ እና ማካዎ እንዳይገቡ ነው ማእቀብ የተጣለባቸው፡፡

እንዲሁም በስማቸው የሚንቀሳቀሱ ካማፓኒዎች እና ሰራተኞቻቸውም በቻይና እንዳይቀሳቀሱ ቻይና ከልክላለች፡፡

ላለፉት አራት አመታት ቻይና እና አሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ሲወዛገቡ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በተለይም በንግድ በሆንግ ኮንግ በታይዋን እንደዚሁም በኮሮና ቫይረስ ጉዳይ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ የገቡበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.